top of page
berana.jpg

አገልግሎት OUR MINISTRIES

የቤተክርስቲያን አገልግሎት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን፣እንደ አጽዋማት፣ ታላላቅ በዓላት እና የመሳሰሉትን መርሐግብሮች ጊዜውን ጠብቆ ፕሮግራም በማውጣት ሕዝቡን የሚያገለግል ሆኖ በተጨማሪም ልዩ ልዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶች ዕለቱንና ሰዓቱን  ጠብቀው እንዲፈጽሙ መዘምራኑን፣ ልዑካኑንና ተጓዳኝ አገልጋዮችን የሚመራና የሚቆጣጠር የመንፈሳዊ አገልግሎት ክፍል ነው፡፡

መንፈሳዊ አገልግሎት ምንድን ነው የሚለውን መሰረታዊ ጥያቄ መመለስ በመንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ የሚኖረንን ሚና ለማወቅ የመጀመሪያው እርምጃ ነው፡፡ መንፈሳዊ አገልግሎት ‹‹መንፈሳዊ (Spiritual)›› እና ‹‹አገልግሎት (Service)›› የሚሉትን ቃላቶች የያዘ ሲሆን ‹‹መንፈሳዊ›› የሚለው ገላጭ የአገልግሎቱን ዓላማና መሪ የሚያሳይ ነው፡፡ መንፈሳዊ አገልግሎት ዓላማው የሰው ልጆች ድኅነት ነው፡፡ መሪውም መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ በአጠቃላይ የሰው ልጆች ለመንግስተ ሰማያት እንዲበቁ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ‹‹መንፈሳዊ አገልግሎት›› ሊባል ይችላል፡፡ ይህም የሕይወትን ቃል ያላወቁ ወገኖች እንዲያውቁና እንዲያምኑ ማድረግ፣ ያመኑት ደግሞ እንዲጸኑና መንፈሳዊ ትሩፋትን እንዲሠሩ ማድረግን ያካትታል፡፡

የመንፈሳዊ አገልግሎት መሰረቱ በቅዱሳት መጻሕፍት የተገለጠው የእግዚአብሔር ፈቃድና ፈቃዱን ለመፈጸም የሚያተጋን አምላካዊ መመሪያ ነው፡፡ ከዘመነ አበው ጀምሮ፣ በዘመነ ኦሪትም በቅዱሳን አባቶችና ነቢያት አድሮ የመንፈሳዊ አገልግሎት ተልዕኮንና መመሪያን የሰጠው በፍፁም አንድነትና በልዩ ሦስትነት የሚመሰገን አምላካችን እግዚአብሔር ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስም ከሦስቱ አካላት አንዱ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ከእመቤታችን ድንግል ማርያም ተወልዶ፣ ግዕዘ ህፃናትን ሳያፋልስ በትህትና አድጎ፣ መንፈሳዊ አገልግሎት ምን መምሰል እንዳለበት በተግባር አስተምሮ ለቅዱሳን ሐዋርያት አብነት የሆነ የአገልግሎት ተልዕኮና መመሪያ ሰጥቷቸዋል፡፡ አብነት የሆነው ተልዕኮ ‹‹እኔ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ›› የሚለው ሲሆን መሪ መመሪያው ደግሞ ‹‹ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብ የዋሆች ሁኑ›› የሚለው ታላቅ ቃል ነው  (ማቴ 10፡16)፡፡ ጌታችን ይህንን ተልዕኮና መመሪያ የሰጠው ለጊዜው ለደቀ መዛሙርቱ ሲሆን ኋላም በእነርሱ እግር ተተክተው በመንፈሳዊ አገልግሎት ለሚሳተፉ ሁሉ ነው፡፡

ታዳጊ ወጣቶች

Youth

ወጣትነት ከሕፃንነት ወደ ዐዋቂነት በሚደረገው ሽግግር ወቅትአንድን ሰው ለዐዋቂነት የሚያሸጋግሩ ስነልቦናዊ፣ አካላዊ፣ማህበራዊና አዕምሮአዊ ለውጦች የሚከናዎኑበት ጊዜ ነው፡፡በወጣትነት ዘመን ከውስጣዊ ፈተና በተጨማሪ ውጫዊ ፈተናየራሱ የሆነ ተጽዕኖ አለው፡፡ የተሻለ የዐዋቂነት ሕይወትለመምራት አንድ ወጣት እነዚህን ፈተናዎች በአሸናፊነትመወጣት አለበት፡፡ ቅድስት ቤተክርስቲያን በዚህ ወሳኝ ሂደትውስጥ ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖራት እሙን ነው፡፡ በዚህ መልኩልጆቿን ኮትኩታ ባሉበት ፈታኝ ዘመን ፈተናውን ተቋቁመው ማለፍእንዲችሉ ማገዝ ከቻለች ለመንፈሳዊ ክብር ልታበቃቸውትችላለች፡፡ በምላሹም ከወጣቶች የሚጠበቀውን መጠነ-ሰፊአገልግሎት ማግኘት ይቻላል፡፡
20200418_233309.jpg
ሰንበት ት/ቤት 
Sunday School

 

ሰንበት ትምህርት ቤት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጉብዝናቸው ወራት ፈጣሪያቸውን እንዲያስቡ የተጻፈላቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል የሚያምኑ እና የሚታመኑ ወጣቶች በጉብዝናቸው ወራት ፈጣሪያቸውን ያስቡ ዘንድ በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ደረጃ ተጠሪነቱ ለሰበካ ጉባኤው ሆኖ የተደራጀ የወጣቶች የትምህርት፣ የጥናትና ምርምር እና የጸሎት ማዕከል ነው፡፡

ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ስለ ቤተክርስቲያን አደረጃጀት እና መዋቅራዊ አሠራር፣ ስለ ክብረ ክህነት እና ስለ ሌሎች የቤተ ክርስቲያን ቀኖናዊ ሥርዓቶች፣ ስለበጎ ፈቃደኝነት እና ስለ አገልግሎት ዋጋ እንዲሁም ስለ ቃለ-ዓዋዲውም ሆነ ሌሎች ቀኖናዊ መጻሕፍት በቂ እውቀት እንዲኖራቸው ከተደረገ አገልግሎቱ ስሙር እና ውጤታማ የማይሆንበት ምንም ምክንያት የለም፡፡

IMG-ac3eb19c3fff1989ddb153639ac16819-V.j

Follow Us

  • YouTube
  • c-facebook

© 2026 by Mekane Hiwot Saint Micheal EOTC

bottom of page